“የሚፈልጉት የእምነት
ቃል ነው”
ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖሊስ
Copyright © 2013 Human Rights
Watch
All rights reserved.
Printed in the United States of
America
Cover design by Rafael Jimenez
Human Rights Watch is dedicated
to protecting the human rights of people around the
world. We stand with victims
and activists to prevent discrimination, to uphold political
freedom, to protect people from
inhumane conduct in wartime, and to bring offenders to
justice. We investigate and
expose human rights violations and hold abusers accountable.
We challenge governments and
those who hold power to end abusive practices and
respect international human
rights law. We enlist the public and the international
community to support the cause
of human rights for all.
Human Rights Watch is an
international organization with staff in more than 40 countries,
and offices in Amsterdam,
Beirut, Berlin, Brussels, Chicago, Geneva, Goma, Johannesburg,
London, Los Angeles, Moscow,
Nairobi, New York, Paris, San Francisco, Sydney, Tokyo,
Toronto, Tunis, Washington DC,
and Zurich.
For more information, please visit our website: http://www.hrw.org
ሂዩማን ራይትስ
ዎች ጥቅምት 2006ዓ.ም
“የሚፈልጉት የእምነት ቃል ነው”
ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ
ፖሊስ ጣቢያ
የሪፖርቱ ይዘት ባጭሩ .................................................................................................................
1
የማሻሻያ ሃሳቦች ........................................................................................................................
5
ለኢትዮጵያ መንግስት ........................................................................................................................
5
ለኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ...................................................................................................
5
ለኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ....................................................................................................................
6
ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን .......................................................................................................
6
ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን .....................................................................................................
7
ለለጋሹ
ማሕበረሰብ ..........................................................................................................................
7
የሪፖርቱ ይዘት ባጭሩ
አንዱ (ፖሊስ) በያዘው ረዥም ጥቁር ዱላ ከኋላ ጭንቅላቴን መታኝ ከዚያ አይኔን
በጨርቅ
አሰረኝ፤ በመቀጠል ወደ ቢሯቸው ወሰዱኝ፤ ይህንን ያደረጉት መርማሪዎቹ ናቸው…ደጋግመው
በጥፊ መቱኝ፡፡ የምነግራቸውን ለመስማት መርማሪዎቹ ዝግጁ አይደሉም፤ በጥቁሩ
ዱላ እና
በጥፊ ደግመው መቱኝ። እዚያው ክፍል እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አቆዩኝ፤ በጣም
ተዳክሜ
ነበር። ከዚያ ወደ ታሰርኩበት ክፍል መለሱኝ እና ሌላ ሰው ወሰዱ፡፡ በሁለተኛው
ቀን
ምርመራ ድብደባው የባሰ ነበር። የሚፈልጉት ጥፋተኛ ነኝ ብየ እንዳምን ነው
፡፡
በ2003ዓ.ም ዓመት አጋማሽ ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ ጋዜጠኛ - ናይሮቢ፣
ሚያዚያ 2004ዓ.ም
በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መሃል ከአንድ ሆቴል እና አንድ የኦርቶዶክስ
ቤቴክርስቲያን አጠገብ በመላ ሃገሪቱ በጣም
ታዋቂ የሆነ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛል።ይህም የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ
ዘርፍ ሲሆን በተለምዶ ማዕከላዊ
በመባል ይታወቃል። ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ሰልፍ አደራጆች፣
በብሄር የተደራጁ አማፅያንን
ይደግፋሉ የሚባሉ ሰዎች እና ሌሎችም በርካታ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች
ሲያዙ በቅድሚያ የሚወሰዱት ወደ ማዕከላዊ
ነው፡፡ ማዕከላዊ ከገቡ በኋላ ምርመራ ይካሄድባቸዋል። በአብዛኞቹ ላይ ደግሞ
ሁሉም ዓይነት እንግልት እና በደል
የሚደርስባቸው ሲሆን ይህም ማሰቃየትን ይጨምራል፡፡
በማዕከላዊ የሚገኙት መርማሪ ፖሊሶች ታሳሪዎች ጥፋታቸውን እንዲያምኑ፣ እንዲናገሩ
ወይም ሌላ መረጃ እንዲያወጡ
የሚያደርጉት በሃይል የማስፈራራት መንገድን በመጠቀም ሲሆን ይህም እስከ ማሰቃየት
እና ሌላ ጎጂ አያያዝ እስከ መፈጸም
ይደርሳል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እስረኞች ከጠበቃ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናገኙ
አይፈቀድላቸውም፡፡ እስረኞቹ
የመርማሪዎቹን ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርጉት ትብብር መጠን በቅጣት ወይም
በማበረታቻ መልክ የውሃ፣የምግብ፣
የመብራት እና የሌሎች አስፈላጊ ነገሮች አቅርቦት ሊከለከሉ ወይንም ሊፈቀድላቸው
ይችላል፡፡
ይህ ሪፖርት ከ2002 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በማዕከላዊ
የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን፣ ህገወጥ
የምርመራ ዘዴዎችን እና የታሳሪዎችን ሁኔታ የሚዳስስ ነው፡፡ ለዚህ ሪፖርት
ሂዩማን ራይትስ ዎች ከ35 በላይ ቀድሞ
ማዕከላዊ ታስረው የነበሩ ግለሰቦችን እና ቤተሰቦቻቸውን ቃለ መጠይቅ አድርጓል፡፡
ምንም እንኳ ሂዩማን ራይትስ ዎች
ማዕከላዊን መጎብኘት ባይችል እና ይህም ሁኔታውን በቀጥታ ለመታዘብ እና በአሁኑ
ወቅት በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን
ለማነጋገር እንዳይችል ቢያደርገውም የዚህ ሪፖርት አዘጋጆች በተለያዩ መንገዶች
የተመረጡት የቀድሞ ታሳሪዎች የሰጧቸውን
መረጃዎች በተናጠል በተደረጉ ቃለ መጠይቆች ለማመሳከር ችለዋል።
በኢትዮጵያ በፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ስለሚፈጸሙ በዘፈቀደ የማሰር፣
የማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝን የተመለከቱ
ወቀሳዎችን መስማት አዲስ አይደለም፡፡ ሆኖም በተለይ ከአወዛጋቢው የ1997
ዓ.ም. ምርጫ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት
ሃሳብን የመግለጽ ነፃነት፣ የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብቶች ላይ የሚያደርገውን
ገደብ በማጠናከር ተቃውሞን ለማዳፈን
የሚያስችሉ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ ይህም የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎችን፣
ጋዜጠኞችን እና ሌሎች ለመንግስት
ያልወገነ ድምፅ የሚያሰሙ ወገኖችን ይዞ ማሰር፣ እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች
ክትትል ሥራ እና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነትን
በእጅጉ የሚገድቡ ህጎችን በሥራ ላይ ማዋልን ይጨምራል፡፡
ከ2001ዓ.ም ጀምሮ አዲስ የወጣው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ በተለይ የመናገር
ነጻነትን ለመገደብ ትልቅ ጉልበት ያለው
መሳሪያ ሆኗል፡፡ በአዋጁ የተካተቱ ድንጋጌዎች ክስ ሳይመሰረት በእስር ላይ
ለረዥም ጊዜ በእስር ያለመቆየት እና ነጻ የፍርድ
ሂደት የማግኘት መሰረታዊ የህግ ከለላዎችን ይጻረራሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
ለተወሰኑ በተለይ ደግሞ በፖለቲካ ረገድ ጥንቃቄ
ሊደረግባቸው ይገባል ለሚባሉ ጉዳዮች ማዕከላዊ ዋና የማሰሪያ እና የምርመራ
ማካሄጃ ቦታ ሆኗል፡፡ በጣም ታዋቂ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ይህንን ህግ ጥሰዋል ተብለው
የተያዙ ሰዎች ጉዳያቸው እስኪመረመር
ወይም ፍርድ ቤት እንዲቀርብ እስኪዘጋጅ ድረስ ማዕከላዊ ታስረው እንዲቆዩ
ተደርገዋል፡፡
ማዕከላዊ አራት የተለያዩ ዋና የማሰሪያ ክፍሎች (ብሎኮች) ያሉት ሲሆን ሁሉም
ቅፅል ስሞች አሏቸው። በየብሎኮቹ ያለው
ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ የተለያየ ነው፡፡ አብዛኞቹ የቀድሞ ታሳሪዎች በምርመራ
ሂደት ወቅት ከአንዱ ብሎክ ወደ ሌላው
እንዴት
ይዘዋወሩ እንደነበር እና ለመርማሪዎቹ ከሚያደርጉት ትብብር በተያያዘ የአያያዛቸው ሁኔታ እንዴት እንደሚለያይ
ለሂዩማን ራይትስ ዎች አብራርተዋል፡፡ በተለይ “ጨለማ ቤት” እና “ጣውላ
ቤት” በመባል በሚታወቁት ክፍሎች ያለው
ሁኔታ እጅግ በጣም አስከፊ ነው፡፡ የጨለማ ቤት ታሳሪዎች የቀን ብርሃን እና
የመፀዳጃ ቤት አገልግሎት የሚያገኙት ውሱን
በሆነ ሁኔታ ሲሆን አንዳንድ ጊዜም ለብቻ ተነጥለው እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡
በጣውላ ቤት ደግሞ ከክፍል ለመውጣት ያለው
እድል የተገደበ ሲሆን ክፍሎቹ በተባይ የተጠቁ ናቸው፡፡ ስሙን ከዓለም ዓቀፉ
ሆቴል ወዳገኘውና “ሸራተን” በመባል
ወደሚታወቀው ብሎክ መዛወር የተሻለ እንቅስቃሴ የማድረግ እንዲሁም ከጠበቃ
እና ከቤተሰብ ጋር የመገናኘት እድልን
ስለሚያስገኝ ታሳሪዎቹ ከእስር ከመለቀቅ ቀጥሎ እጅግ የሚናፍቁት ነገር ነው።
የማዕከላዊ ሃላፊዎች በዋናነትም መርማሪ ፖሊሶች እስረኞቹን በተለያየ መንገድ
ያሰቃያሉ፤ ጎጂ አያያዝም ይፈጽማሉ፡፡
ታሳሪዎቹ በጥፊ፣ በእርግጫ፣ በቦክስ እንዲሁም በብትር እና በሰደፍ በተደጋጋሚ
እንደተመቱ ለሂዩማን ራይትስ ዎች
ገልፀዋል፡፡ የተወሰኑት እጆቻቸውን ከኮርኒስ ጋር ታስረው እንዲንጠለጠሉ አሊያም
ደግሞ እጆቻቸው ከጭንቅላታቸው በላይ
ታስረው እየተደበደቡ ለረጅም ሰዓታት እንዲቆሙ እንደተደረጉ ገልጸዋል። ታሳሪዎች
እጃቸው በሰንሰለት ታስሮ በክፍላቸው
ውስጥ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ይደረጋሉ። አንድ ሰው ለአምስት ተከታታይ ወራት
በዚህ ሁኔታ የቆየበት አጋጣሚ አለ።
በምርመራ ወቅት የማስፈራሪያ ቃላትን ይሰነዘሩባቸዋል፡፡ እንዳንዶቹም ማሰቃየት
ሊባል በሚችል ደረጃ ለብቻ ተነጥለው
ለረዥም ጊዜ ያቆያሉ።
በእስር ቤቱ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታም ታሳሪዎቹ ዘርዝረዋል። ከእነዚህም መካካል
በቂ የምግብ አቅርቦት እንደሌለ፣ የቀን
ብርሃን ማግኘት ላይ ጥብቅ ገደብ እንዳለ፣ አስከፊ የንፅህና እና ውሱን የህክምና
አገልግሎት የሚጠቀሱት ናቸው፡፡በተለይ
በመጀመሪያው የምርመራ ወቅት ያለው ሁኔታ አስከፊ ነው፡፡
የማዕከላዊ ሃላፊዎች አስገዳጅ የምርመራ ዘዴዎችን አስከፊ ከሆነው የእስር
ሁኔታ ጋር በማዳመር የሚጠቀሙት በታሳሪዎቹ
ላይ ያለውን ጫና ለመጨመር እና ታሳሪዎቹ እንዲናገሩ፣ እንዲያምኑ አሊያም
ትክክለኛ ሆነም አልሆነ መረጃ እንዲያወጡ
ለማድረግና ከዚያም ራሳቸውንም ሆነ ሌሎችን በወንጀል እንቅስቃሴ ተሳትፈዋል
ለማሰኘት ነው። አንዳንድ ጊዜ በዚህ
መንገድ የተገኘን የእምነት ቃል ታሳሪዎች ከተለቀቁ በኋላ የመንግስት ደጋፊዎች
እንዲሆኑ ለማስፈራሪያነት ወይም ደግሞ
ፍርድቤት በታሳሪዎቹ ላይ በማስረጃነት ያቀርቡታል፡፡
የቀድሞ ታሳሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በመጀመሪያዎቹ የእስር ሳምንታት የህግ
ጠበቃም ሆነ የቤተሰብ አባላትን እንዲያገኙ
እንደማይፈቀድላቸው ለሂዩማን ራይትስ ዎች ተናግረዋል፡፡ አንዳንዶቹ በእስር
በቆዩባቸው ወራት በሙሉ በምንም መልኩ
ከሰው ጋር እንዲገናኙ አይፈቀድላቸውም፡፡ በምርመራ ወቅት የህግ ጠበቃ አለመኖሩ
ታሳሪዎቹ ላይ የሚፈፀመውን
ማንገላታት እንዲጨምር ያደርጋል፣ በመርማሪዎቹ የሚፈጸሙ ጎጂ አያያዞችንና
ማሰቃየትን የሚመለከቱ መረጃዎች
እንዳይመዘገቡ ያደርጋል፣ እንዲሁም ፍርድ ቤት ይህ ያልተገባ አያያዝ እንዲሻሻል
መፍትሔ ሊሰጥ የሚችልበትን እድል
ይገድባል፡፡ በማዕከላዊ የሚገኙ መርማሪ ፖሊሶች በብሔራዊና ዓለማቀፍ ደረጃ
እውቅና የተሰጣቸውንና ለታሳሪዎች ሊደረጉ
የሚገባቸውን በማስገደድ የተገኘን ቃል በፍርድ ቤት በማስጃነት ከማቅረብ መቆጠብን
የመሳሰሉ መሠረታዊ የህግ ጥበቃዎች
ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸው በዚህ መልክ መሰናክል ይፈጥራሉ።
ታሳሪዎቹ ለሚደርሱባቸው ችግሮች መፍትሄ ሊያገኙ የሚችሉባቸው መንገዶች ውሱን
ናቸው፡፡ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ
የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ገለልተኛነት አይንጸባረቅባቸውም፡፡ እስረኞቹ ማዕከላዊ
ስለተፈጸሙባቸው የማሰቃየት ድርጊቶች
እና ጎጂ አያያዞች ፍርድ ቤት አቤቱታቸውን ሲያሰሙ አቤቱታ የቀረበላቸው ፍርድ
ቤቶች ሁኔታው እንዲስተካከል አጥጋቢ
እርምጃ አይወስዱም፡፡ አብዛኞቹ የቀድሞ ታሳሪዎች ወደ ማዕከላዊ ሲመለሱ መርማሪዎቹ
ሊያደርሱባቸው የሚችለውን
የበቀል እርምጃ በመፍራት ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ስለደረሰባቸው ያልተገባ አያያዝ
እንደማይናገሩ ለሂዩማን ራይትስ ዎች
ገልፀዋል፡፡ ሌሎቹ ጭራሽ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡
ማዕከላዊን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የማሰሪያ ቦታዎች ባለው የሰብዓዊ
መብቶች ሁኔታ ላይ በመንግስታዊ
አካላት የሚደረገው ክትትል ውስን ነው።በተመሳሳይ መልኩ በገለልተኛ አካላት
የሚደረግ በቂ ክትትልም የለም፡፡
ለመንግስት ቀረቤታ ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተወካዮች እና
ሌሎች ባለስልጣናት ማዕከላዊን ጎብኝተው
በዚያ ስላለው የእስረኞች አያያዝ ሁኔታ በይፋ እና በግል በተደረጉ ግንኙነቶች
አንዳንድ አሳሳቢ ያሏቸውን ጉዳዮች
አንስተዋል፡፡ ነገር ግን የቀድሞ ታሳሪዎች ለሂዩማን ራይትስ ዎች እንደተናገሩት
የኮሚሽኑ ተወካዮች ጉብኝት ባደረጉበት
ወቅት
በማዕከላዊ ሃላፊዎች ታጅበው የነበረ መሆኑንና ከጉብኝቱ በኋላም በተጨባጭ የተሻሻለ ነገር የለም፡፡
ላለፉት አስር ዓመታት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች የሃገር ውስጥ እና
ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች በመላ
ኢትዮጵያ በሚገኙ በይፋ በሚታወቁ እና በይፋ በማይታወቁ እስር ቤቶች በዘፈቀደ
የሚደረግ እስር ፣ጎጂ አያያዝ፣ እንዲሁም
ማሰቃየትን ጨምሮ ለተራዘመ ጊዜ የሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን
የሚመለከቱ መረጃዎችን በማጠናቀር ይፋ
አድርገዋል። መንግስት እነዚህን ግኝቶች አልተቀበለም ወይም ደግሞ ተዓማኒነት
የሌላቸውን የራሱን ምርመራዎች አድርጓል።
ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች መሰረት
የኢትዮጵያ መንግስት የሚጠበቅበትን
ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ የመወጣት እና የሰብዓዊ መብቶች ፖሊሲዎችን በሰነድ
የመቅረፅ አወንታዊ ርምጃዎችን ወስዷል፡፡
በ2002 ዓ.ም የማሰቃየት፣ የጭካኔ፣የኢሰብዓዊ ወይንም ክብርን በሚያዋርድ
መልኩ የሚደረግ አያያዝ ወይንም ቅጣትን
ማስወገጃ ስምምነትን ተፈጻሚነት ለሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት
የባለሙያዎች ኮሚቴ ኢትዮጵያ
የመጀመሪያውን ሪፖርቷን አቅርባለች፡፡
መንግስት ከ2005 እስከ 2007ዓ.ም የሚዘልቅ ብሄራዊ የሰብዓዊ መብቶች
የድርጊት መርሃ ግብር ነድፏል፡፡ ሂዩማን ራይትስ
ዎች ረቂቁን እንደተመለከተው ከፍርድ በፊት በእስር ስለሚቆዩ እና በፍርድ
የሚታሰሩ ሰዎችን አያያዝ ሁኔታ ለማሻሻል
የሚያስችሉ ነጥቦች ተካተውበታል፡፡የድርጊት መርሃ ግብሩ ከክስ በፊት በሚኖር
እስር ጊዜ የህግ ጠበቃ የማግኘት ችግር
እንዳለ፣ በቂ የሆነ የቅሬታ ማቅረቢያ መንገድ እንደሌለ፣ የምግብ እና የሕክምና
አቅርቦት ደካማ እንደሆነ፣ እንዲሁም የሌሎች
አገልግሎቶች አቅርቦት ችግር እንዳለ እና ሊስተካከል እንደሚገባው በትክክል
አስፍሯል፡፡
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተለይ ደግሞ ፌዴራል ፖሊስ በማዕከላዊ እና በሌሎች
የማሰሪያ ቦታዎች ዙሪያ በተደጋጋሚ
የሚነሱትን ችግሮች ለመቅረፍ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ እስረኞች
የታሰሩበትን ምክንያት የማወቅ መብትን
ጨምሮ፣ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ የህግ ምክር የማግኘትና በቤተሰቦቻቸው የመጎብኘት
መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው
ማድረግ የሚፈጸሙ በደሎችን ለመቀነስ ይረዳል።
ዓቃቤያነ ሕግ እና ዳኞችም በእስር ላይ ያሉ ሰዎችን አያያዝ በንቃት መከታተል
እንዲሁም የማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝን
በተመለከተ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ያለማንም ባለስልጣን ጣልቃገብነትና አደናቃፊነት
መመርመር ይኖርባቸዋል፡፡
በተጨማሪም በማሰሪያ ቦታዎች ያለውን አያያዝ በተመለከተ በድፍረት የሚናገሩ
እስረኞች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ
ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እና ሰብዓዊ እርዳታ የሚያደርጉ ድርጅቶች እና የዲፕሎማሲ
ማህበረሰብ አባላትን ጨምሮ ገለልተኛ
ብሔራዊ እና ዓለማቀፍ ተቋማት፤ እንደ የማሰቃየት፣ የጭካኔ፣የኢሰብዓዊ አያያዝ
ወይንም ክብርን በሚያዋርድ መልኩ
የሚደረግ አያያዝ ወይንም ቅጣትን ለመከላከል የወጣውን ስምምነት የሚከታተለው
ልዩ ተወካይ እና የዘፈቀደ እስርን
የሚከታተለው የሥራ ቡድን ያሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ
ህብረት የሰብአዊ መብቶች አካላት
ማዕከላዊን እንዲሁም ሌሎች በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶችን ባልተገደበ
ሁኔታ እና አስቀድመው ማሳወቅ ሳይኖርባቸው
መጎብኘት እንዲችሉ ባለስልጣናት መፍቀድ አለባቸው፡፡
በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ለሚቀርቡ ትችቶች መንግስት አብዛኛውን ግዜ የብቃት
ማነስ፣ የስልጠና ወይንም የአቅም እጥረት
ጉዳይ ብቻ እንደሆነ ለማስመሰል ይሞክራል እንጂ በስፋት የሚስተዋለውን ማሰቃየት
እና ጎጂ አያያዝ ለማስቆም
መሰረታዊው ጉዳይ የፖለቲካ ፈቃደኝነት ፣ የጥፋት ፈጻሚዎቹ ተጠያቂነት እና
ለተጎጂዎች ችግሮች መፍትሄ የመስጠት
እንደሆነ ማንሳት አይፈልግም፡፡
ማዕከላዊን በመሳሰሉ ቦታዎች ተጨማሪ ሃብት መመደብ በዚያ የሚታየውን አስከፊ
የአያያዝ ሁኔታ በመጠኑ ሊያሻሽል
ይችላል። ነገር ግን የእስረኞች አያያዝን በተመለከተ እውነተኛ ለውጥ መምጣት
ያለበት በከፍተኛ ደረጃ ከሚገኙ የመንግስት
አካላት ነው፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ እስከ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እና
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ድረስ ያሉት
አመራሮች በእስረኞች ላይ የሚደረግ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ በቀላሉ ታይቶ ሊታለፍ
እንደማይችል ግልጽ መልዕክት
ማስተላለፍ አለባቸው፡፡ይህንን መልዕክትም ህጉን የሚጥሱ ሃላፊዎች ላይ የዲሲፕሊን
ቅጣት እንዲወሰድ በማድረግ እና ክስ
በመመስረት በተግባር መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ወሳኙ ጉዳይ ገለልተኝነቱ
የተረጋገጠ እና ከእስረኞች የሚቀርቡ
ቅሬታዎችን ተቀብሎ ትክክለኛ ፍርድ የሚሰጥ የፍትሕ ተቋም መኖሩ ነው፡፡ በተጨማሪም
የፖለቲካ ተፅዕኖ ያለበት ክሶች
መጀመሪያውኑም እንዳይመሰረቱ ለማድረግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጎ
አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅን
እና
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል አለበት፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በየዕለቱ የሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን
ለማስተካከል በእውነት ቁርጠኝነት ያለው
መሆኑን
ማሳየት የሚችለው እነዚህን እርምጃዎች መውሰድ ሲችል ብቻ ነው፡፡
የማሻሻያ ሃሳቦች
ለኢትዮጵያ መንግስት
ለፌዴራል ፖሊስ እና ማዕከላዊ ለሚመደቡ ህግ አስከባሪ አካላት በሁሉም ታሳሪዎች ላይ
ህገወጥ እስር፣
የማሰቃየት ተግባር እና ጎጂ አያያዝ መፈጸምን እንዲያቆሙ ግልፅ ትዕዛዝ መስጠት
ጎጂ አያያዝን በተመለከተ በሚቀርቡ ሁሉም ቅሬታዎች ላይ ፈጣን፣ ግልፅ እና ገለልተኛ
ምርመራ ማድረግ
እና ጥፋተኛ ሆነው በሚገኙት ላይ ያለምንም የደረጃ ልዩነት የዲሲፕሊን እርምጃ
መወሰድ ወይም ክስ
እንዲመሰረት ማድረግ
ከመጀመሪያው የእስር ጊዜ ጀምሮ የሕግ ባለሙያ ማግኘትና ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ሁሉ
ጠበቃ
እንዲገኝ የማድረግ መብትን ጨምሮ በማዕከላዊና በሌሎች የማሰሪያ ቦታዎች ያሉ
ታሳሪዎች የቤተሰብ
አባላትና የህክምና አገልግሎትን ሳይዘገይ ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታ በከፍተኛ
ደረጃ እንዲሻሻል ማድረግ
በማሰቃየት ወይም በሃይልና ማስፈራራትን በመጠቀም የተገኙ መረጃዎች ለፍርድ ቤት ማስረጃ
ሆነው
እንዳይቀርቡ ማድረግ።ማሰቃየትን ወይም ጎጂ አያያዝን በተመለከተ የቀረበ ቅሬታን
በሚመረምሩበት ወቅት
በዐቃቤ ህግ እና በዳኞች ላይ የሚደረግን ጣልቃ ገብነት ለመከላከል እና ለመቅጣት
የሚያስችሉ
እርምጃዎችን መወሰድ
በዘፈቀደ የተያዙ በተለይ ደግሞ ሃሳብን የመግለፅ ነጻነት፣ የመሰብሰብ እና የመደራጀት
መብቶችን የመሳሰሉ
መሰረታዊ መብቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲተገብሩ የተያዙ እስረኞች ባስቸኳይ
ከእስር እንዲለቀቁና
የተመሰረተባቸውም ማንኛውም ክስ እንዲሰረዝ ማድረግ
የተባበሩት መንግስታት ‘የእስረኞች አያያዝ ዝቅተኛ ድንጋጌዎች’ በሚል ያወጣውን መስፈርት
የማያሟሉ
ማዕከላዊ ውስጥ የሚገኙ የእስር ቦታዎችን መዝጋት
በማዕከላዊ እና በሌሎች የማሰሪያ ቦታዎች ታሳሪዎችን ከሰዎች ጋር እንዳይገናኙ አድርጎ
ማሰር እና ለረዥም
ጊዜ ለብቻ ነጥሎ የማቆየትን ድርጊት ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ
የሰብዓዊ መብቶች ክትትል የሚያደርጉ እና የሰብዓዊ ተራድኦ ድርጅቶች ያለገደብ ሁኔታዎችን
እንዲከታተሉና ከታሳሪዎች ጋር ለብቻ ተገናኝተው እንዲነጋገሩ በመፍቀድ ማዕከላዊ
እና ሌሎች የማሰሪያ
ቦታዎች በገለልተኛ አካላት ክትትል እንዲደረግባቸው ማድረግ
የማሰቃየት፣የጭካኔ፣የኢሰብዓዊ አያያዝ ወይም ክብርን በሚያዋርድ መልኩ የሚደረግ አያያዝ
እና ቅጣትን
ለመከላከል የወጣውን ስምምነት ለሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ልዩ ተወካይ
እንዲሁም የዘፈቀደ
እስርን ለሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት የሥራ ቡድን በማናቸውም ጊዜ ኢትዮጵያን
እንዲጎበኙ
የሚያስችል ግብዣ ማድረግ
በረቂቅ ብሄራዊ የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሃ ግብር ላይ በሰፈረው መልኩ በማዕከላዊ
እና በሌሎችም
የማሰሪያ ቦታዎች የቅሬታ ማቅረቢያ መንገዶች ባስቸኳይ እንዲመቻቹ ማድረግ
የፌደራል ፖሊስ፣ ዐቃቤያነ ሕግ እና ሌሎች ህግ አስከባሪ አካላት የዓለማቀፍ የሰብዓዊ
መብቶች ደረጃን
በጠበቀ መልኩ ተገቢውን የምርመራ ሥራ ስልጠና ማግኘታቸው ማረጋገጥ
የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅን ከኢትዮጵያ
ህገ መንግስት እና
የመደራጀት፣ሀሳብን የመግለጽ እና በሰላም የመሰብሰብ መብቶችን በተመለከተ
ኢትዮጵያ ግዴታ
ከገባችባቸው ዓለማቀፍ ህግጋት ጋር በሚጣጣም መልኩ ማሻሻል
ለኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅን ከኢትዮጵያ
ህገ መንግስት እና
የመደራጀት፣ሀሳብን የመግለጽ እና በሰላም የመሰብሰብ መብቶችን በተመለከተ
ኢትዮጵያ ግዴታ
ከገባችባቸው
ዓለማቀፍ ህግጋት ጋር በሚጣጣም መልኩ ማሻሻል
እስረኞች ባስቸኳይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለማስቻል፣ ከፍርድ በፊት የሚደረግ
የተራዘመ እስርን
ለመከላከል እና በማሰቃየትና በጎጂ አያያዝ የተገኘ የእምነት ቃል ወይም ሌላ
መረጃ በፍርድ ቤት ማስረጃ
ሆኖ እንዳይቀርብ በማድረግ የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓትን ግልፅ ለማድረግ ኢትዮጵያ
ግዴታ የገባችባቸውን
ዓለማቀፍ ህግጋት የሚጻረሩ የወንጀል ስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎችን ማሻሻል
የማሰቃየት፣ የጭካኔ፣የኢሰብዓዊ አያያዝ ወይም ክብርን በሚያዋርድ መልኩ የሚደረግ አያያዝ
እና ቅጣትን
ለመከላከል የተደረገው ስምምነት አማራጭ ፕሮቶኮል የሆነውንና የፕሮቶኮሉ የማሰቃየት
መከላከል ንዑስ
ኮሚቴ ኢትዮጵያን መጎብኘት የሚያስችለውን ሰነድ ማጽደቅ እንዲሁም ቅሬታ አቅራቢዎች
በገለልተኛ
የተባበሩት መንግስታት ኮሚቴ ጉዳያቸው እንዲታይ የሚያስችለውን የዓለም ዓቀፉ
የሲቪል እና የፖለቲካ
መብቶች የቃል ኪዳን ስምምነት አማራጭ ፕሮቶኮል ማጽደቅ
ለኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች
ያልተገባ አያያዝን በተመለከተ እስረኞች የሚያቀርቡት ቅሬታ ከፖሊስ ገለልተኛ በሆነ
አካል በአስቸኳይ እና
በነጻነት እንዲጣራ መደረጉን ማረጋገጥ፤ ያልተገባ አያያዝን በተመለከተ የተሰጠን
የፍርድ ቤት ትዕዛዝ
የማይቀበሉ ወይም ተፈጻሚነቱን የሚያደናቅፉ የመንግስት አካላት ላይ እርምጃ
መውሰድ
ስለተፈፀመባቸው ያልተገባ አያያዝ ቅሬታ ያቀረቡ እስረኞች ላይ የበቀል ርምጃ እንዳይወሰድባቸው
ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ማረጋገጥ
በማሰቃየት ወይም በሌላ ጎጂ አያያዝ የተገኘ ንግግር፣ የእምነት ቃል ወይም ሌሎች መረጃዎች
በማስረጃ
መልክ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ማረጋገጥ ፤ ማስረጃው በሃይል ወይም በማስፈራራት
የተገኘ ስለመሆኑ
ቅሬታ ሲቀርብ ቅሬታውን ለመመርመር እንዲያስችል ቅሬታ የቀረበባቸው አካላት
ለፍርድ ቤቱ የቀረበው
ማስረጃ እንዴት እንደተገኘ የሚገልጽ መረጃ እንዲያቀርቡ ማድረግ
ከፍርድ በፊት የሚደረግ እስር ዓለማቀፍ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ በልዩ ሁኔታ ብቻ
የሚፈጸም መሆኑን
እና ለአጭር ጊዜ ብቻ መሆን እንዳለበት ይህንንም ዐቃቤያነ ሕግ ተጠርጣሪዎችን
በእስር ለማቆየት
የሚያስችል በቂ ምክንያት ያላቸው መሆኑን እንዲያሳዩ በማድረግ ማረጋገጥ
ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
በማዕከላዊ እና በሌሎች ማሰሪያ ቦታዎች የሚገኙ ክስ ያልቀረበባቸው እና ፍርድ ቤት
ያልቀረቡ እስረኞችን
ባስቸኳይ መፍታት። ክስ የቀረበባቸው ተጠርጣሪዎች ያልዘገየ ፍትሃዊ እና ግልጽ
የፍርድ ሂደት
ማግኘታቸውን ማረጋገጥ
ከፍርድ ሂደት በፊት የሚደረግ እስር የዓለም ዓቀፍ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ በልዩ
ሁኔታ የሚፈጸም
መሆኑን ማረጋገጥ
በማዕከላዊ የሚገኙ የፌደራል ፖሊስ መርማሪዎች እና ሌሎች ሃላፊዎች አሰራር ላይ የሚደረግ
ቁጥጥር
እንዲጠናከር ማድረግ። በየጊዜው በቦታው እየተገኙ ጉብኝት ማድረግ፣ለታሳሪዎች
ስለሚደረገው አያያዝ
እና ስለ እስር ቤቱ ሁኔታ በግል እና በሚስጥር እስረኞቹን ማነጋገር እንዲሁም
ጎጂ አያያዝን እና ማሰቃየትን
በተመለከተ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በገለልተኝነት ማጣራት
በማዕከላዊ እና በሌሎች የማሰሪያ ቦታዎች የሚደረግን ከሰው ጋር እንዳይገናኙ አድርጎ
የማሰር እና
ለተራዘመ ጊዜ ለብቻ ነጥሎ የማቆየት ድርጊቶችን ለማስቆም የሚያስችል እርምጃ
መወሰድ
በማዕከላዊ እና በሌሎች የፌዴራል ማሰሪያ ቦታዎች የሚገኙ እስረኞች ያልተገባ አያያዝን
አስመልክቶ
በየጊዜው የሚያቀርቡትን ቅሬታ የሚያሳይ ስታቲስክስ ዝርዝር መውጣት እንዲሁም
ለቀረቡ ቅሬታዎች
የተሰጡ ምላሾችን፣ በፈፀሙት ህገወጥ ድርጊት ምክንያት ምን ያህል ፖሊሶች
ከስራ እንደታገዱ፣ ክስ
እንደተመሰረተባቸው ወይም ሌላ የዲሲፕሊን ቅጣት እርምጃ እንደተወሰደባቸው
የሚያሳይ ግልጽ ሪፖርት
ማቅረብ__
ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ማዕከላዊ እና ሌሎች የማሰሪያ ቦታዎችን አዘውትሮ እና ያለ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መጎብኘት፤
በግል እና
ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ታሳሪዎችን ማነጋገርና ያልተገባ አያያዝን በተለመከተ
በቀረቡ ቅሬታዎች ላይ
ክትትል ማድረግ
ስርዓት ባለው ሁኔታ የማዕከላዊ እስረኞችን የሚመለከቱ የፍርድ ሂደቶችን መከታተል እንዲሁም
በተለይ
ታሳሪዎች ያልተገባ አያያዝን በተመለከተ ለሚያቀርቡት ቅሬታ የሚመለከታቸው
አካላት የሚሰጡትን
ምላሽ መከታታል፣ ቅሬታ አቅራቢዎች በማዕከላዊ ወይም ወደ ሌሎች የማሰሪያ
ቦታዎች ሲዛወሩ
ሊፈፀምባቸው የሚችሉ የበቀል እርምጃዎችን መከታተል
ለለጋሹ ማሕበረሰብ
በማዕከላዊ እና በሌሎች በኢትዮጵያ ወስጥ በሚገኙ የማሰሪያ ቦታዎች ታሳሪዎች ላይ የሚፈጸሙ
የማሰቃየት፣ የጎጂ አያያዝ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ
ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ
በይፋም ሆነ በግል በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ማሳሰብ፡፡
የሚፈፀሙትን በደሎች
ለማስቆም እና አጥፊዎቹን ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ፖሊሲ እንዲቀርፁ በተለይ
የፌዴራል ጉዳዮች
ሚኒስትር፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር እና የፍትህ ሚኒስትር
ላይ ግፊት ማድረግ
በማሰሪያ ቦታዎች የሚፈጸሙ በደሎችን በተመለከተ በሚቀርቡ ቅሬታዎች ላይ አፋጣኝ፣ ግልጽ
እና
ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ በይፋ ማሳሰብ
የሰብዓዊ መብቶችና የሰብዓዊ ተራድኦ ድርጅቶች እንዲሁም ዲፕሎማቶች ማዕከላዊን እና
ሌሎች የማሰሪያ
ቦታዎችን ለመጎብኘት የሚያስችል ያልተገደበ ፈቃድ እንዲኖራቸው በርትቶ መጠየቅ
የማሰቃየት፣የጭካኔ፣የኢሰብዓዊ አያያዝ ወይም ክብርን በሚያዋርድ መልኩ የሚደረግ አያያዝ
እና ቅጣትን
ለመከላከል የተደረገውን ስምምነት ተፈጻሚነት የሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት
ልዩ ተወካይን
ጨምሮ ሌሎች የተባበሩት መንግስታት እና የአፍሪካ ሕብረት የሰብዓዊ መብቶች
ተካታታይ አካላት
ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ እንዲጋበዙ የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ማሳሰብ
በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት የተያዙ ተከሳሾችን የችሎት ውሎ መከታተል እና ተከሳሾቹ
ለህዝብ
ክፍት በሆነ ችሎት የመዳኘት መብታቸው እንዲከበር ለባለስልጣናቱ ጥሪ ማስተላለፍ
የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ እና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ማሻሻያ
እንዲደረግባቸው ጥሪ
ማስተላለፍ
No comments:
Post a Comment